የቢሮው ኃላፊ መልዕክት

አቶ ብርሃኑ ጎሽም

የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ኃላፊ

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ፣ህገ-መንግስቱንና ህገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን የማስከበር፣የዜጎችን ሰብዓዊ መብቶች የማስከበር፣የወንጀል ሕጎችን የማስፈፀም፣የወጡ ህጎችን ተፈጻሚነት የማረጋገጥ፣የሚያወጣቸው ህጎች ላይ እና የሚወስናቸው ትላልቅ ውሣኔዎች ላይ የክልሉን መንግስት የማክበር፣የመንግስትና የሕዝብ መብትና ጥቅም የማስጠበቅ ትልቅ ኃላፊነት ተሰጥቷል፡፡

ይህንን ኃላፊነቱን በአግባቡ የሚወጡ እና በህዝብ ዘንድ ታማኝነትና ተቀባይነት ያለው ተቋም ለመፍጠር የፍትሕ ትራንስፎርሜሽን እቅድ በማቀድ አዳዲስ ህጎችን በማዘጋጀት፣ነባር ህጎችን በማሻሻል፣አደረጃጀቶችን በማጠናከር፣አዳዲስ የአሰራር ስርዓቶችን በማዘጋጀት ሕዝብንና መንግስት የሚጠብቁትን ፈጣን፣ተደራሽ እና ጥራት ያለው የፍትሕ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በሂደቱም ወንጀለኛን የማስቀጣት፣በወንጀል የተወሰደን ሃብት የማስመለስ፣የመንግስትንና የሕዝብን ጥቅም የማስጠበቅ፣ጥራት ያላቸውን ህጎች የማዘጋጀት፤ ተቋሙን ምቹና ሳቢ የማድረግ፣ተቋማዊ ተደራሽነትን የማስፋት፣አመራሩንና ባለሙያውን የማብቃት ስራዎችን ለማከናወን ችሏል፡፡

ይህንን ተግባር ለማከናወን በየደረጃው ያላችሁ የተቋማችን አመራሮች እና ባለሙያዎች የጎላ ድርሻ ስለነበራችሁ ምስጋና ይገባችኋል፡፡ ስለሆነም ተግባራችን በአንድ ወቅት ተሰርቶ የሚጠናቀቅ ባለመሆኑ የጀመርነውን የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራን አጠናከሮ በማስቀጠል በሕዝብ ዘንድ ታማኝነትና ተቀባይነት ያለው ተቋም ለመገንባት በየደረጃው የምትገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች ሙሉ አቅማችሁን፤ጊዜያችሁን እና እውቀታችሁን ከላቀ መልካም ሥነ-ምግባር ጋር በማቀናጀት የተጣለባችሁን ኃላፊነት ልትወጡ ይገባል፡፡

ስለ ቢሮው

በ2022 የሕዝብ አመኔታ ያለው እና በሀገር ደረጃ ተምሳሌት የሆነ የፍትሕ ተቋም ሆኖ ማየት፤

ቀልጣፋ፤ ውጤታማ  እና ተደራሽ  የፍትሕ አገልግሎት በመስጠት  የሕግ የበላይነትን በማስከበር ሰብአዊ መብትን፣ ሰላምና ደህንነትን እንዲሁም የመንግስትንና የህዝብን ጥቅም ማረጋገጥ፤ 

  • ገለልተኝነት፣ ነፃነትና ተጠያቂነት
  • የሕግ የበላይነት እና ሰብዓዊ መብቶች ላይ የጸና እምነት
  • የህዝብ አገልጋይነት
  • ሙያዊ ብቃት
  • የቴክኖሎጅ ተጠቃሚነት

ዜናዎች | News

ዋና ዋና አገልግሎቶች

ያግኙን

Contact Form
Please write your name
Please write your e-mail address
Please write your messages
Scroll to Top